MOU-Ministry-of-Labor-and-Skills-1

ሕብረት ባንክና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ እድል ፈጠራ የፋይናንስ አማራጭን ማስፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ሕብረት ባንክና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ እድል ፈጠራ የፋይናንስ አማራጭን ማስፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ 

ሕብረት ባንክ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥቅል የፋይናንስ አገልግሎቶች አቀርቦትና አተገባበር ላይ የተመሠረተ የስትራቴጂያዊ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመገኘት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ዓላማ በሚኒስቴሩ እና በባንኩ መካከል የትብብር ማዕቀፍ በመዘርጋት ለምሩቃን፣ ለሰልጣኞች፣ ለአዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎች (Startups)፣ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች (MSMEs)፣ ለውጭ አገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች እና ለውጭ አገር ሠራተኞች የፋይናንስ ተደራሽነትንና ሥራ ፈጠራን በጋራ ለማሳደግ፣ እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ባላቸው መስኮች ተቋማዊ ትብብርን ለማጠናከር ነው።

በስምምነቱ ወቅት የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር ሕብረት ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ እና ይህ ስምምነትም የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ጋር የሚሰራቸውን ሥራዎች እንደሚያጠናክር አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላችው ከሕብረት ባንክ ጋር የተደረሰው ስምምነት እምቅ አቅም ኖሯቸውና መስራት እየቻሉ በገንዘብ አቅርቦት አለመመቻቸት ምክንያት ወደ ሥራ መሰማራት ያልቻሉ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀው ሕብረት ባንክ ይህን ሀገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የሥራ እድል ፈጠራ የፋይናንስ አማራጭ ስምምነቱን የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተፈራረሙ ሲሆን በስምምነት ፕሮግራሙ ላይ የሁለቱ ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts