ሕብረት ባንክ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
ሕብረት ባንክ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት አድርጓል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የገንዘብ ድጋፉን ያበረከቱት የሕብረት ባንክ ሲኒየር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ማሕበሩ ለሚሰራቸው ሰብዓዊ ሥራዎች አመስግነው የማሕበሩ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም የበጐ አድራጎቱን ሥራ በሥፋት እንዲሰራ የሚረዳውን የሕንፃ ግንባታ መደገፍ ለባንኩ ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ፅገሬዳ አክለውም ሕብረት ባንክ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን በዚህ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚገኝና ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተደረገው የገንዘብ ድጋፍም የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ተስፋሚካኤል ታፈሰ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሰሜን አዲስ አበባ ለሚያስገነባው ሁለገብ የሰብአዊ አገልግሎት መስጫ ህንፃ ግንባታ የህብረት ባንክ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ በራሴና በቀይ መስቀል ማህበሩ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ያሉ ሲሆን ማህበሩም እየሰጠ ያለውን የሰብአዊ አገልግሎት አሁን ካለበት ደረጃ በማሻሻል ለሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና ራዕይውን ለማስፋት የእያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
በመርሐ -ግብሩ ላይም ሕብረት ባንክ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው ሁለገብ ህንፃ ግንባታ ገቢ ማሳባሰቢያ ፕሮግራም ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የሕብረት ባንክ ሲኒየር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅገሬዳ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋሚካኤል ታፈሰን ጨምሮ የባንኩና የማሕበሩ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ