ሕብረት ባንክ ላየንስ ክለብን በመቀላቀል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ባንክ ሆነ

ሕብረት ባንክ እየሰጠ ከሚገኘው የፋይናንስ አገልግሎት ባሻገር በተለያዩ የማሕበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ የሚሳተፍ ሲሆን ይህንንም ለማጠናከር የአለም አቀፉ የላይንስ ክለብ አባል ሆኖ እውቅና አግኝቷል፡፡

ከሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የማኔጅመንት አባላት መካከል 32ቱ የላየንስ ክለብ አባል የሆኑ ሲሆን እነዚህን አባላት በይፋ ወደ ክለቡ ለመቀላቀልና ስራ ለማስጀመርም ላየንስ ክለብ ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የእራት ግብዣ አከናውኗል፡፡ በዚህ ደማቅ የመመስረቻ መርሀግብር ላይ አባላቱ ‘’የሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የማኔጅመንት ላየንስ ክለብ’’ በሚል ስያሜ ተመስርተው የክለቡ የክብር ፒን ተበርክቶላቸዋል፡፡ አባላቱም ላየንስ ክለብ የሚያደርገውን የበጎ አድራጎት ተግባር ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡

በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የማኔጅመንት አባላት ላየንስ ክለብ ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ ተቋማዊ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ላየንስ ክለብ ባንኩ ይህን ስራ የሚያጠናክርበትን መንገድ ስላመቻቸ አመስግነዋል፡፡ በተጨማሪም የላየንስ ክለብ መርህ የሆነው ‘’እናገለግላለን’’ (’’we serve’’) እና የሕብረት ባንክ መርህ የሆነው ‘’በሕብረት እንደግ’’ (‘’United We Prosper’’) ያላቸውን የአላማ ትስስር አንጸባርቀዋል፡፡ በመመስረቻ መርሀግብሩ ላይ የተለያዩ የላየንስ ክለብ አባላት እና ባለሀብቶች ተገኝተዋል፡

አለም አቀፉ የላየንስ ክለብ በሕብረተሰቡ ውስጥ የነጻ አገልግሎት እና የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የመሳተፍ ልምድን በማዳበር አለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት የሚሰራ ትልቅ ክለብ ነው፡፡

Similar Posts