ሕብረት ባንክ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ‘’ኩላሊት ጤና፣ ሕይወት ተስፋ’’ በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ ተሳተፈ::





ሕብረት ባንክ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ‘’ኩላሊት ጤና፣ ሕይወት ተስፋ’’ በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ ተሳተፈ::
ሕብረት ባንክ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ‘’ኩላሊት ጤና፣ ሕይወት ተስፋ’’ በሚል መሪ ቃል ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያና የግንዛቤ ማስጨበጫ የሩጫ ውድድር ላይ ተሳትፎ አድርጓል፡፡
ከባንክ ሥራው ባሻገር ሕብረተሰቡን የሚጠቅሙ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመደገፍ የሚታወቀው ሕብረት ባንክ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የመጀመሪያ ደረጃ የሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታውን አስመልክቶ በተዘጋጀው የድጋፍ ማሳበሳቢያ የሩጫ ውድድር ላይ ተሳትፏል፡፡ ከዚህ ቀደምም ባንኩ ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ተግባራትን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በሩጫ ውድድሩ ላይ ከሕብረት ባንክ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተዉጣጡ ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!