ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ የዕድሮች ጥምረት ም/ቤት የውይይት መድረክ ላይ ተሳተፈ

ሕብረት ባንክ የኢትዮጵያ የዕድሮች ጥምረት ም/ቤት መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት በባንኩ እየተሰጡ ባሉ የባንክ አገልግሎቶች ዙሪያ ለታዳሚዎች ገለፃ አድርጓል፡፡

ባንኩ ስለሚሰጣቸው አጠቃላይ አገልግሎቶች ገለፃ ያቀረቡት የባንኩ ሪሌሽንሺፕ ማናጀር አቶ ያሬድ በቀለ ባንኩ ለዕድሮች ጥምረት ም/ቤት ምቹ የሚሆኑ አገልግሎቶችን ይዞ መቅረቡን አሳውቀዋል፡፡ አቶ ያሬድ አክለውም ባንኩ ከአዲስ አበባ ዕድሮች ም/ቤት ጋር በቅርበት አብሮ ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀው፤ ይህንን ተሞክሮ ወደ ክልል የዕድር ጥምረቶች በማድረስ በጋራ አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዕድሮች ጥምረት ም/ቤት ሰብሰቢ አቶ ታምራት አበበ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ከሁሉም ባንኮች ቀደሞ ዕድሮችን በመቅረብ አብሮ ለመስራት ስላሳየው ተነሳሽነት አመስግነው የየክልሉ የዕድሮች ጥምረት አባላትም ከባንኩ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከተለያዩ የክልል ከተሞች የመጡ የዕድር ጥምረት ተወካዮች፣ የኦ.ኤስ.ኤስ.ኤች.ዲ (OSSHD) ተወካዮች እና ሌሎችም እንግዶች የተገኙ ሲሆኑ ባንኩ እየሰጣቸው ባለው አገልግሎቶች ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ሕብረት ባንክ

በሕብረት አንደግ!

Similar Posts