ሕብረት ባንክ በ2025/26 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 5.46 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለጸ።
የሕብረት ባንክ 29ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄደ፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሳቢ አቶ መስፍን ተሰማ እንደገለጹት የ2025/26 የበጀት ዓመት ሕብረት ባንክ ከታክስ በፊት 5.46 ቢሊዮን ብር ያተረፈ መሆኑን እና ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ4.71 ቢሊዮን ብር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ አክለውም በበጀት ዓመቱ የሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ማስፋፍያ ግንባታን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሕጋዊ ፍቃዶች እና ሰነዶች የተገኙ መሆኑን እና በዚህም መሰረት የዲዛይን ሥራው ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ የቁፋሮው ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ለጉባኤው አሳውቀዋል፡፡
በቀረበው ሪፓርት መሰረት በበጀት ዓመቱ መዝጊያ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት የ36.70 ቢሊዮን ብር (32.22%) ዓመታዊ እድገት በማስመዝገብ 150.63 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል የ37.96% ወይም የ4.66 ቢሊዮን ብር እድገት በማስመዝገብ 16.95 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ፤ ይህም በቀጣዩ የበጀት ዓመት ሊከናወኑ የታቀዱትን የአሰራር ልሕቀት የማረጋገጥና የገበያ ማስፋፋት ሥራዎችን የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ የደንበኞቹን ቁጥር በማሳደግ እና የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 124 ቢሊዮን ብር አድርሷል፡፡ ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ31.3 ቢሊዮን ብር ወይም የ33.78 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ታውቋል፡፡ ከወለድ ነፃ ፋይናንስን ጨምሮ አጠቃላይ የባንኩ የብድር ክምችት 99.49 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
የበጀት ዓመቱ ሕብረት ባንክ ትልቅ ለውጥ ያደረገበት እና በቀጣይም ባንኩ ተግዳሮቶችን በማሸነፍ ራዕዩን ለማሳካት ብቃት ያለው ግዙፍ ባንክ መሆኑን ያረጋገጠበት መሆኑን በጉባኤው ተገልጿል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!






