ሕብረት ባንክ አመታዊ የስራ አመራር ጉባኤውን አከናወነ

ሕብረት ባንክ አመታዊ የስራ አመራር ጉባኤውን አከናወነ ሕብረት ባንክ የ2021/2022 አመታዊ የስራ አመራር ጉባኤውን "You can't spell HIBRET without I, Our Bank's success is on our hand" በሚል መሪ ቃል ከሀምሌ 19-20 2014 ዓ/ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አከናውኗል፡፡ በጉባኤው ላይ የተጠናቀቀው በጀት አመት የስራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በአዲሱ በጀት አመት እቅድ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችም የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶች ተበርክተዋል፡፡ በጉባኤው ላይ የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

#Hibretbank #ሕብረትባንክ

Similar Posts