ሕብረት ባንክ እና ሞኔታ ቴክኖሎጂስ አክሲዮን ማህበር በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ሕብረት ባንክ እና ሞኔታ ቴክኖሎጂስ አክሲዮን ማህበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ጥር 25 ቀን 2015 ዓም በሕብረት ባንክ ዋና መሥርያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ እና የሞኔታ ቴክኖሎጂስ አክሲዮን ማህበር የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሳምሶን ጌቱ ናቸው፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት ቴክኖሎጂን በማጎልበት የፋይናንስ አካታችነትን እና ተደራሽነትን በማስፋት እድገትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው፡፡ ሕብረት ባንክ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ከተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በጋራ እየሰራ ሲሆን ከሞኔታ ቴክኖሎጂስ አክሲዮን ማህበር ጋር የተፈረመው ስምምነትም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ የሚያስቀጥል ነው፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts