1-EDI-MOU

ሕብረት ባንክ እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር የሚገኘው ኢንተርፕረነርሺፕ ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት (EDI) የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ሕብረት ባንክ እና ኢንተርፕረነርሺፕ ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት (Entrepreneurs Development Institutes) በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (MSME) እንዲሁም ለሥራ ፈጣሪዎች (startups) የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋት እና የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ተቋማቶቹን የማብቃት ሥራ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተጨማሪም የንግድ ፕሮፖዛሎችን በመቅረፅ በጋራ ፈንድ የማፈላለግ፣ በኮርፖሬት ደረጃ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ እና ሲስተም ዲቨሎፕመንት (Business Development Service and System Development Training) ስልጠና ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ የማርኬቲንግ እና ስትራቴጂ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ደረጀ ከበደ እና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር) ሲሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts