ሕብረት ባንክ እና ትረስትድ ቴክ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ሕብረት ባንክ እና ትረስትድ ቴክ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ጳጉሜ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ሀይሉ እና የትረስት ቴክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ናቸው፡፡ሕብረት ባንክ ከትረስትድ ቴክ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ደንበኞች የላኪ ፔይ ፕላትፎርምን በመጠቀም አለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውሮችንና ልዩ ልዩ ሀገር አቀፍ የክፍያ ሥራዎችን በጋራ መስራት እንዲችሉ ማድረግን ያለመ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts