ሕብረት ባንክ እና ዘ ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን / The Inspired Ethiopian Youth Association / የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
ሕብረት ባንክ እና ዘ ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን/ The Inspired Ethiopian Youth Association / በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ሀይሉ እና የ ዘ ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን / The Inspired Ethiopian Youth Association/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ልዩነህ ታምራት ናቸው፡፡
ሕብረት ባንክ ከ ዘ ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን/ The Inspired Ethiopian Youth Association/ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በዋናነት የወጣቶች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ!
በሕብረት እንደግ!