ሕብረት ባንክ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡

ሕብረት ባንክ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡
ሕብረት ባንክ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በጋራ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ይፋ ማድረጊያ ሪፖርት አቀራረብ (Reporting Framework for Climate-Related Disclosure) ላይ ያተኮረ ስልጠና ከግንቦት 4-5 ቀን 2018 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መስርያ ቤት ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው የባንኩን አቅም የሚገነባና ለብሔራዊ ባንክና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ይፋ ማድረጊያ ሪፖርት አቀራረብ አቅምን የሚያሳድግ መሆኑም በስልጠናው ወቅት ተገልጿል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ አማካሪ ድርጅት በሆነው ዲኤአይ (DAI) ሲሆን ስልጠናው የአየር ንብረት ስጋት አስተዳደርና የግሪን ፋይናንሲንግ ላይ ግንዛቤ መፍጠርንና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ይፋ ማድረጊያ ሪፖርት አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
ለሁለት ቀናት በቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከሕብረት ባንክ የተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!