ሕብረት ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ የዕድሮች ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ
ሕብረት ባንክ ዛሬ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ከተማ የዕድሮች ምክር ቤት ተወካዮች ጋር በባንኩ ዋና መ/ቤት የጋራ ምክክር አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የባንኩ የስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አንዷለም ኃይሉ እንደገለፁት ሕብረት ባንክ በሕብረት ሰርቶ ማደግን መርህ ያደረገ ባንክ እንደመሆኑ መጠን የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ከዕድሮች ጋር በመስራት በአብሮነት ረጅም ርቀት ለማጓዝ ያለመ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ዕድሮች በተለያየ መልኩ አባሎቻቸውን የሚደግፉ ከመሆኑ አንፃር ሕብረት ባንክ ይሄንን ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባሕልን ይበልጥ ለማሳደግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የዕድሮች ምክር ቤት ተወካዮችም ሃሳብ የሰጡ ሲሆን፤ ባንኩ የቀረቡትን ሀሳቦች ግብዓት በማድረግ ቀጣይነት ያለው ትብብርን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን በመንደፍ ሁለቱ አካላት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ