ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ግንቦት 23 ቀን 2ዐ16 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡ የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዷለም ሐይሉ እና የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳለው ሞሲሳ ናቸው፡፡

በስምምነቱም ላይ የሕብረት ባንክ የስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዷለም ሐይሉ እንደገለፁት ሕብረት ባንክ ሁሉን አካታች በመሆን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የሚገኝ ለ25 ዓመታት ኢትዮጵያዊ ማንነትን ይዞ እየተጓዘ ያለ ባንክ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ሕብረት ባንክ በቴክኖሎጂ ተጠቃሽ በመሆን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋርም በአጋርነት በመሥራት ዘላቂ ግንኙነትን እያዳበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳለው ሞሲሳ በበኩላቸው ከሕብረት ባንክ ጋር የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን በሚያበረታቱ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀው በዚህም ረገድ ባንኩ ከባለሥልጣኑ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ቀደሚ በመሆኑ አመስግነዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክና የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts