ሕብረት ባንክ የሕብር ሞባይል ባንኪንግ መተግበርያን ለሕብረተሰቡ የማስተዋወቅ ሥራ በይፋ አስጀመረ
ሕብረት ባንክ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በተገኙበት በሕብር ታወር የሕብር ሞባይል መተግበርያን የማስተዋወቅ ዘመቻ ይፋዊ የማብሰሪያ ፕሮግራም አከናውኗል፡፡
ሕብረት ባንክ በራሱ አይቲ ቡድን አዲሱን/ Latest Version/ የሞባይል ባንኪንግ እና የ *811# ዩ.ኤስ.ኤስ.ዲ/USSD/ የካቲት 3ዐ ቀን 2015 ዓ.ም. መተግበሩ የሚታወስ ሲሆን ይህንን መተግበርያ የባንኩ ደንበኞችና ብሎም ሕብረተሰቡ በስፋት መጠቀም እንዲችሉ የሞባይል መተግበርያውን የማስተዋወቅ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የሕብር ሞባይል መተግበርያ የማስተዋወቅ ዘመቻውን በይፋ ያስጀመሩት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ሁላችንም የሕብር ሞባይል መተግበሪያን የማስተዋወቅ አደራ አለብን ያሉ ሲሆን ቅርንጫፎች ከዲስትሪክቶች ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩና መተግበሪያውን ለደንበኞች የማስተዋወቅ ሥራን በስፋት እንዲያከናውኑ አበክረው ተናግረዋል፡፡ ሕብረተሰቡም ሕብረት ባንክ በራሱ የአይቲ ቡድን ያበለፀገውን ሕብር የሞባይል ባንኪንግ እና የ *811# ዩ.ኤስ.ኤስ.ዲ/USSD/ በመጠቀም ቀልጣፋና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከይፋዊ ማብሰሪያ ፕሮግራሙ ባሻገርም ከዲስትሪክትና ከቅርንጫፎች ለተውጣጡ ሠራተኞች የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የሕብር ሞባይል መተግበርያ የማስተዋወቅ ዘመቻ ከመስከረም 15 እስከ ጥቅምት 19 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ሕብረት ባንክ!
በሕብረት እንደግ!!