ሕብረት ባንክ የሴቶች ቀንን አከበረ

የሴቶች ቀን “የሕብረት ሴት ነኝ” በሚል መሪ ቃል በሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ወ/ሮ ሂሩት አዳሙ ሁላችንም በሴትነት ውስጥ ያለውን የፈጣሪ ትልቅ ጥበብ እና በረከትም በመረዳት በጐ ተጽዕኖ በመፍጠርና የሚጠበቅብንን ሀላፊነት በመወጣት ለተሻለ ነገ በሕብረት እንስራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክብርት አምባሳደር ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንም ባካፈሉት የሕይወት ተሞክሮ እና ሥልጠና #ሴቶች በጎደሏቸው ነገሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ ያሏቸውን ፀጋዎች በመቁጠርና በመጠቀም እራሳቸውን መርምረው ማወቅ፣ በፍትሃዊነት መብታቸውን ማስጠበቅ እና በራሳቸው በመተማመን ሕይወታቸውን በዓላማና በዕቅድ መምራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በሕብረት ባንክ ለ4ኛ ጊዜ በተከበረው በዚሁ በዓል ላይ የባንኩ የስራ አመራሮች፣ የዋና መ/ቤት እና የቅርንጫፍ ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ሕብረት ባንክ በሕብረት እንደግ!!

Similar Posts