ሕብረት ባንክ የሽያጭ ቅስቀሳ መርሃ ግብር አስጀመረ፡፡
ሁልጊዜም ደንበኞችን በማገልገል እና በማስደሰት የሚታወቀው ሕብረት ባንክ “ማፍራት ፣ መልሶ ማንቀሳቀስ እና ማሳደግ; “Acquire Re-engage, and Grow” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ለአንድ ወር የሚቆይ የሽያጭ ቅስቀሳ/Sales Campaign/ መርሃ ግብር አስጀመረ፡፡ የሽያጭ ቅስቀሳ /Sales Campaign/ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር በሚገኘው በሕብር ታወር ቅርንጫፍ ተካሂዷል፡፡
በመረሃ ግብሩ ላይ የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሄር እንደተናገሩት እስካሁን ሲደረጉ የነበሩ የገበያ ቅስቀሳዎች ጥሩ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም ከሚከናወኑት የሽያጭ ቅስቀሳ መርሃ ግብሮች በተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ፣ በዲጂታል ባንኪንግ እና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ጥሩ ግብአት እንደሚገኝ እና የጀመርነውን የከፍታ ጉዞ ማስቀጠያ መንገድ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ አክለውም በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ ደንበኞችን አመስግነው ፍሬያማ የሽያጭ ቅስቀሳ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
የባንኩ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሳኒ ቦቸሬ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክትም ለአንድ ወር በሚቆየው የሽያጭ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር ላይ ሁሉም ሠራተኛ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ያሉ ሲሆን የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካትም የሁሉም ድጋፍ እና ሀሳብ አስፈለጊ መሆኑን አፅንኦተ በመስጠት የሥራ ባህል ለውጥን እና የባንኩን ዕይታ ለመገንባት የሁላችንም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!




