ሕብረት ባንክ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የባንኩ ቅርንጫፎች እውቅና ሰጠ

ሕብረት ባንክ በተያዘው በጀት አመት የግማሽ አመት አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የባንኩ ቅርንጫፎች የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም በሸራተን አዲስ ሆቴል እውቅና ሰጥቷል፡፡

በእውቅና አሰጣጥ ዝግጅቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ እውቅና የተሰጣቸው ቅርንጫፎች የባንኩ ኩራት መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም ይህን ውጤታማነት አጠናክሮ ማስቀጠል እና በሁሉም ቅርንጫፎች ተመሳሳይ ውጤት ማስመዘገብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሕብረት ባንክ ቢዝነስ እና ኦፕሬሽንስ ሲኒየር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ በበኩላቸው እውቅና የተሰጣቸው ቅርንጫፎች ፈታኝ የሆነውን ሀብት የማሰባሰብ ስራ በሚገባ በመወጣት ለሌሎች ቅርንጫፎች ተምሳሌት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግበሩ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts