|

ሕብረት ባንክ የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በራሱ የአይቲ ቡድን ተገበረ

ሕብረት ባንክ በራስ አቅም ያሻሻለውን የ *811# ዩኤስኤስዲ ኮድ /USSD Code/ እና የሞባይልባንኪንግ መተግበሪያ /application/ የብሔራዊ ባንክ ተወካይ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ይፋ አድርጓል፡፡

መተግበሪያውን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀውን የማብሰሪያ ፕሮግራም በንግግር የከፈቱት የሕብረት ባንክዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ሕብር የሞባይል መተግበሪያ ባንኩ ሲጠቀምበት የነበረውን*811# USSD/ ዩኤስኤስዲ ኮድ በማሻሻልና አዳዲስ አገልግሎቶችን በማከል የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መተግበሪያው በባንኩ ባለሙያዎች በራስ አቅም የለማ መሆኑና በርካታ አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑደግሞ የተለየ እንደሚያደርገውና በዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለሌሎች ባንኮችና ለሀገር አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን በመወከል በእንግድነት የተገኙት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያስርዓት ክትትልና ልማት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ዳምጠው በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገርአቀፍ ደረጃ የዲጂታል የክፍያ ስርዓትን ለማሻሻልና የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶእየሰራ መሆኑንና ባንኮችም በዚሁ ስራ ላይ በመሳተፋቸው በዲጂታል የክፍያ አገልግሎት አሰጣጥ እድገት እየታየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር ሳምራዊት ጌታመሳይ የማብሰሪያ መርሀግብሩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት ዛሬ የተዋወቀውን ሕብር የሞባይል መተግበሪያ ለማልማት የተኬደበት ርቀት ባንኩ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡ ወደፊትም ባንኩ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ቀዳሚ ለመሆን በትጋት እንደሚሰራ ገልጸው ይህን ስራ በትጋት ለተወጡ የባንኩ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አዲሱ ሕብር የሞባይል መተግበሪያ የባንኩን ገጽታ በጠበቀና የተለያዩ ዘመናዊ አገልግሎቶችን ባከተተ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ ሕብረት ባንክ በሀገራችን የባንክ ኢንዱስትሪ በራስ አቅም የሞባይል መተግበሪያ አልምቶ ተግባር ላይ በማዋል ቀዳሚ ባንክ ሲሆን በኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ማኔጅምነት ሲስተምም የ ISO/IEC 27001:2013 ተሸላሚ የሆነና አስተማማኝ ደህንነቱ የተመሰከረለት ባንክ ነው፡፡

በሕብረት እንደግ!

#HibirMobile

Similar Posts