ሕብረት ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አኖረ::
ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛልሕብረት ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አኖረ::
ሕብረት ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት አጠገብ በሚገኘው የህንፃው ግንባታ ቦታ ላይ አከናወነ፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ተሰማ እንደተናገሩት ሕብረት ባንክ በአሁኑ ወቅት ስትራቴጂውን እንደገና በመቃኘት የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት በሚያስችሉት ተግባራት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ እና ይህም የዋና መ/ቤት ሕንፃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ያለምንም አላስፈላጊ መዘግየት ወደ ተግባር መግባቱ የዚሁ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም መጪው ጊዜ ሕብረት ባንክ ያካበተውን የረጅም አመታት ልምድ ወደ ስኬት የሚቀይርበት፣ ስሙን በሚመጥን ልክ አገልግሎቱን የሚያዘምንበት እና በፋይናንስ ኢንደስትሪ ውስጥ ራሱን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም የሚያስከብር ሥራ የሚሠራበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመሰረት ድንጋዩን በክብር ያስቀመጡት አቶ ዛፉ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ እየተገበረ ያለውን የለውጥ ሂደት አድንቀው መጪው ጊዜ ለባንኩ ብሩህ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ የዲዛይን ሥራውን በሠራው በእስክንድር አርክቴክትስ በተሰጠው ገለፃ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታው በ3,255 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚያርፍ እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው ዘመናዊ ሕንፃ ሲሆን ለመኖሪያ አፓርትመንቶች፣ ለሱቆች፣ ለቢሮዎች እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚውል ታውቋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!













