ሕብረት ባንክ የይቀበለ፣ ይመንዝሩ ይሸሇሙ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ መርሃ ግብር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎችን ሸለመ

ሕብረት ባንክ ሇስድስት ወራት ሲያካሂድ በቆየው የይቀበለ፣ ይመንዝሩ ይሸሇሙ የውጭ ምንዛሬ ማበረታቻ መርሃ ግብር የሎተሪ ዕጣ የወጣላቸው አሸናፊዎችን በባንኩ ዋና መስርያ ቤት ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ሸልሟል፡፡

ባንኩ አሸናፊ ሇሆኑ ባሇ ዕደሇኞች አውቶሞቢል ፣የባሇ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች፣ ቴሌቪዥኖችና ስማርት ሞባይል ሰልኮች አበርክቷል፡፡

የሕብረት ባንክ ደንበኞችን ተሸላሚ ያደረገበት ይኸው የይቀበለ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸሇሙ መርሃ ግብር የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማበረታት በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ያራሱን የሆነ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው፡፡

ባንኩም ሇወደፊቱም ተመሳሳይ የሎተሪ መርሃ ግብሮችን በማከናወን በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማስፋትና የቁጠባ ባህልን የማጎልበት ዕቅድ ሇማሳካት ያላሰሇሰ ጥረት ያደርጋል፡፡

ባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ሇማሳደግና የውጭ ምንዛሬን በባንኩ የሚቀበለና የሚመነዝሩ ደንበኞችን ሇማበረታት የይቀበለ፣ ይመንዝሩ ይሸሇሙ የሎተሪ ዕጣ ማውጣት መርሃግብር ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎች

» የሕብረት ባንክ የቅርንጫፍ ብዛት 380 ደርሷል
» ባንኩ በኦንላየን ባንኪንግ አስተማማኝነትና ደህንቱ የተጠበቀ አገልግሎት በመስጠት
» ከአሇም አቀፉ PECB MS ድርጅት የISO/IEC 27001:2013 ሰርተፊኬት አግኝቷል

Similar Posts