ሕብረት ባንክ የ2023/24 የበጀት አመት የስራ አፈጻጸሙን በአመርቂ ሁኔታ አጠናቀቀ!

እንኳን ደስ አላችሁ!

ሕብረት ባንክ የ2023/24 የበጀት አመት የስራ አፈጻጸሙን በአመርቂ ሁኔታ አጠናቀቀ!

ሕብረት ባንክ እ.ኤ.አ የ2023/24 የበጀት አመት የስራ አፈጸጸሙን በአመርቂ ሁኔታ ማጠናቀቁን አስመልክቶ የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መለኩ ከበደ ከሕብረት ባንክ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት ጋር በመሆን ስኬቱን ያከበሩ ሲሆን፤ ዋና ስራ አስፈጻሚው በነበራቸው ቆይታ የአመራር አባላቱን እና መላው የሕብረት ባንክ ሰራተኞችን በበጀት አመቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በድል በመሻገር እጅግ በጣም አመርቂ ውጤት በማስመዝገባቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም አዲስ በተጀመረው የስራ ዘመን ባንኩ ከፊቱ የሚኖሩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶችን ተቋቋሞ በድል ለመገስገስ የሚያስችለውን እቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፤ መላው ሰራተኛ ለዚሁ እቅድ ስኬት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ “ እንደተለመደው በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ድል እንዘጋጅ” በማለት ለአዲሱ የስራ ዘመን መላው የባንኩ ሰራተኞች እና አመራሮች እንዲዘጋጁ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts