ሕብረት ባንክ የ3ተኛውን ዙር “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎች ሸለመ፡፡
ሕብረት ባንክ ባካሄደው የ3ተኛው ዙር “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” መርሃ ግብር እጣ የወጣላቸውን ባለዕድለኞች ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋናው መስርያ ቤት ሸልሟል፡፡
በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ ሲኒየር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ተስፋዬ እንደተናገሩት ይህ መርሃ ግብር ለሃገራችን ከሚያስገኘው የውጭ ምንዛሬ ባሻገር ዜጎች በህጋዊ መንገድ ተጠቅመው ገንዘባቸውን እንዲቀበሉና እንዲመነዝሩ ከማበረታታቱም ባሻገር ሀገርን መጥቀም የሚቻልበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ወ/ሮ ፅጌሬዳ አክለውም ባንኩ ለወደፊቱም የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የተሻለ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በሽልማቱ አንድ (1) የቤት አውቶሞቢል፣ ሁለት (2) ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ሶስት (3) የውሃ ፓምፕ ፣ ሶስት (3) ፍሪጆች፣ ሶስት (3) የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ፣ ሶስት (3) ስማርት ቴሌቪዢኖች፣ሶስት (3) የዉሀ ማጣሪያ ማሽኖች እና አምስት (5) ስማርት ስልኮችን ለእድለኞች የተበረከቱ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ እድለኞችም በተመሳሳይ በባንኩ የክልል ቅርንጫፎች ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
ሕብረት ባንክ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግ ብሎም የባንኩን የተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግ አልሞ ከነሀሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ያዘጋጀው የ” ይቆጥቡ፤ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ“ መርሃ ግብር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ መከናወኑ ይታወሳል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!