ሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉን በፓናል ውይይት አጠናቀቀ
ሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የክብረ በዓሉ ማጠቃለያ የሆነው የፓናል ውይይትም “The impact of Macro Economic Factors on the Performance of Ethiopian commercial Banks” በሚል ርዕስ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ተከናውኗል፡፡
የፓናል ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስጀመሩት የሕብረት ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ ባንኩ በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን በመቋቋም በካፒታል መጠኑ፣ በትርፋማነቱ፣ በሀብት መጠኑ፣ በደንበኞች ቁጥር፣ በብድር መጠን፣ በቅርንጫፍ ብዛት እና የሠራተኞቹን ቁጥር በማሳደግ በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ ትልልቅ የግል ባንኮች አንዱ መሆን መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ባንኩ 25ኛ አመት በዓሉን ሲያከብር የ25 አመታት ጉዞውን ከመዘከር ባለፈ ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን፣ የባንኩ አመራሮች እና ሠራተኞች የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ በደም እጦት ምክንያት ሕይወታቸው አደጋ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ደም በመለገስ ሰብአዊ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ የሚሆን የአንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ አስታውሰዋል፡፡
በሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ አጋፋሪነት በተከናወነው በዚህ የፓናል ውይይት ጥሪ የተደረገላቸው የሀገራችን ምሁራን፣ ባለአክሲዮኖች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አመራሮች፣ ደንበኞች፣ የሚዲያ አካላት እንዲሁም የሕብረት ባንክ አመራሮች እና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱም በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አውጪዎች እና ተቀባዮች መካከል የሚኖሩ ልዩነቶችንና በልዩነቶች ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉትን ስጋቶች በመዳሰስ እና የመፍትሄ አቅጣጫን በማመላከት ተጠናቋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ መረጃ እንዲደርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም: https://t.me/HibretBanket
ሊንክዲን: https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/HibretBank
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/hibretbank/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/@hibretbanket
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/