ተፈርመው ዋጋቸው ስላልተከፈለባቸው አክሲዮኖች ክፍያ ማስታወቂያ
የሕብረት ባንክ አ.ማ. 10ኛው የባለአክስዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩን ካፒታል ወደ ብር 5,000,000,000.- (ብር አምስት ቢሊዮን) እንዲያድግ በወሰነው መሰረት የአክሲዮን መግዣ ማመልከቻ ቅጽ ላይ በመፈረም ለመግዛት ካመለከቱት አክስዮኖች ውስጥ ከፍያ ያልተፈፀመባቸውን አክሲዮኖች የመክፈያ ጊዜ ተጠናቋል:: ስለሆነም ቀሪ ክፍያ ያለባችሁ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በንግድ ሕጉ አንቀፅ 289 በተደነገገው መሰረት ከፍያ ያልተፈፀመባቸውን አክሲዮኖች ዋጋ ከግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀን ጊዜ ውስጥ በሕብረት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት አክሲዮን አስተዳደር ክፍል በመቅረብ ክፍያ እንድትፈፅሙ እናሳውቃለን፡፡ በተጠቀሰው 15 ቀን ጊዜ ውስጥ ከፍያ ያልተፈፀመባቸውን አክሲዮኖች በንግድ ሕጉ በተደነገገው እና የባለአክስዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ተፈፃሚ እንደሚሆን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
የሕብረት ባንክ አ.ማ.
የዳይሬክተሮች ቦርድ