እንኳን ደስ አለን! ሕብረት ባንክ ዓለምአቀፍ የISO/IEC 27001:2013 የኦዲት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጠው!!!

ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች የISO/IEC 27001:2013 ሰርተፊኬት በማግኘት ቀዳሚ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም ባንኩ በኦንላየን ባንኪንግ፣ በዳታ ሴንተርና በዲዛስተር ሪከቨሪ ፋሲሊቲ የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ማኔጅምነት ሲስተም የISO/IEC 27001:2013 መስፈርትን በማሟላት አስተማማኝ የደህንነት ስርዓት መዘርጋቱን ለማስመስከር ችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎም ዓለም አቀፉ PECB MS ድርጅት በተቀመጡ የISO/IEC 27001:2013 መስፈርቶች መሰረት የባንኩን የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ሲስተም ኦዲት በማድረግ ለሕብረት ባንክ የመጀመሪያ ዙር የኦዲት ማረጋገጫ ሰጥቶታል ፡፡

ባንካች ላገኘው የኦዲት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰማውን ደስታ እየገለጸ እንዲህ ያሉ ጥንቃቄዎች በሀገራችንና በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያግዝና ፣ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የሚረዳ ብሎም ደንበኞቻችን አስተማማኝ የሆነ የኦንላየን ባንኪንግ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑ ለወደፊቱም ቀጣይነት ባለው መልኩ በዚህ ረገድ ባንኩ ጥረቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts