የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ 

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.ወ/ሮ ፍቅርተ ተስፋሁን አሳየአቶ ዮሃንስ ታደሰ ተሰማበሻሌአዲስ አበባ ከተማ፣ንፋስ ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣የቦታ ስፋት 235 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ባለሁለት ፎቅ ቤት  
 
 
AA000081108442
 
 
34,109,210.00
የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2.አቶ መኑር ጣሰው  ወ/ሮ የሺ ዘርጋ በረዳ አራዳ ሻሸመኔ 
ሻሸመኔ ከተማ፣ቡርቃ ጉዲና ክ/ከተማ፣ቀበሌ 06 ፣የቦታ ስፋት 370 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ  የሆነ  ቤት
 20108 
5,251,610.00
የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
3.አቶ ጠናቸው ኮቶላ ጩሉቄአቶ ቱሉ ገመቹቡሌሆራ ቢሻን ጉራቻ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 175  ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት 
OR111010418006
4,753,476.00የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
4.አቶ አብይ ታደለ ሲማ አቶ አብይ ታደለ ሲማ ሀዋሳ ሻሸመኔ ከተማ፣አቦስቶ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 03፣ የቦታ ስፋት 316.60 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ  የሆነ  ቤትB/0204 
4,295,033.55
መጋቢት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ  ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡ 
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት  ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡የሌሎች ንብረቶች ጨረታ ደግሞ የሚካሔደውንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች  ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ያመቻቻል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- በሻሌ ቅርንጫፍ 0116 67 08 40፣ አራዳ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ፡ 0462 11 44 45፣ ቡሌሆራቅርንጫፍ፡ 0464 43 16 48፣ ሀዋሳቅርንጫፍ፡ 046 220 42 68 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ: 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts