የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ 

ተራ ቁ.የተበዳሪ ስምየአስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋትየንብረት ይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥርየሐራጅ መነሻ ዋጋ የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብርሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1.ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማ/ ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግ/ማ/ሸገርአዲስ አበባ ከተማ፣አራዳ ክ/ከተማ፣ወረዳ 09፣የቦታ ስፋት 852.6 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለድርጅት የሆነ በግንባታ ላይ ያለ ሕንፃ፤  
 
 
 
አ/ሊዝ/17/08/6362/01
 
 
 
355,897,544.00
ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
2.አቶ ፀሐይ አንዱአለም  ጥሩነህ አቶ ፀሐይ አንዱአለም  ጥሩነህ አቡነ ጴጥሮስ 
አዲስ አበባ ከተማ፤አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፤ወረዳ 08፣ የቦታ ስፋት 313 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 
 AA000070802136/2157 
 21,301,112.00
ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት
አቶ ፀሐይ አንዱአለም  ጥሩነህአቶ ፀሐይ አንዱአለም  ጥሩነህአቡነ ጴጥሮስአዲስ አበባ ከተማ፤አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፤ወረዳ 08፣የቦታ ስፋት 171 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ G+3 ቤት 
AA000070805457
17,201,656.00ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
3.አቶ አብዮት በዳዳ ቡታአቶ አብዮት በዳዳ ቡታሞጆ ሞጆ ከተማ፣ቄራ ቀበሌ፣የቦታ ስፋት 253.62 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤትOR021022406009 
3,343,248.00
ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
4.አቶ መኑር ጣሰው  ወ/ሮ የሺ ዘርጋ በረዳ አራዳ ሻሸመኔሻሸመኔ ከተማ፣ቡርቃ ጉዲና ክ/ከተማ፣ቀበሌ 06፣የቦታ ስፋት 370 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት201085,251,610.00ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
5.አቶ አብይ ታደለ ሲማ  አቶ አብይ ታደለ ሲማ  ሀዋሳ ሻሸመኔ ከተማ፣አቦስቶ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 03፣የቦታ ስፋት 316.60 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ  የሆነ  ቤትB/0204 
4,295,033.55
ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት
6.አቶ ጠናቸው ኮቶላ ጩሉቄአቶ ቱሉ ገመቹቡሌሆራ ቢሻን ጉራቻ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 175  ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤትOR1110104180064,753,476.00ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
7.አቶ አባው ገብሬ ውድነህአቶ ምናለ ጨምር አድማሱጃዊጎጃም፣ጃዊ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 223  ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለድርጅት  የሆነ  ግንባታ107/07579,744.00ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
8.አቶ ውበት ባዜ ደሴአቶ ውበት ባዜ ደሴባህርዳርጎጃም፣ዱርቤቴ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ  የሆነ  ግንባታ9682/2012693,875.00ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡ 
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ከተራ ቁጥር 1-2  ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች  ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ከተራ ቁጥር 3-6 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ የሚካሄደውንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡የሌሎች ንብረቶች ጨረታ የሚካሄደው ባህርዳር ከተማ፣ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና(ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ነው፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች  ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ ሸገር ቅርንጫፍ ፡ 011 126 5462፣ አቡነ ጴጥሮስ ቅርንጫፍ: 011 126 6131፣ ሞጆ  ቅርንጫፍ: 022 116 0162፣ አራዳ ሻሸመኔቅርንጫፍ፡ 046 211 4445፣ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ፡046 220 4268 ፣ ቡሌሆራ ቅርንጫፍ፡ 046 443 1648፣ ጃዊ ቅርንጫፍ 058 278 0495፣ ባህርዳርቅርንጫፍ 058 222 1203 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts