የሕብረት ባንክ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
“ኢትዮጵያን እናልብስ” የሚለውን ሃገራዊ ራዕይ በመደገፍ የሕብረት ባንክ አመራር አባላትና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ማኖር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በየካ ሚሊኒየም ፖርክ አካሄደዋል፡፡
የባንኩ ሰራተኞች በእለቱ 1,500 ሀገር በቀል ችግኞችን የተከሉ ሲሆን በቀጣይነትም የተተከሉትን ችግኞች ለመንከባከብ ቃል ገብተዋል፡፡ የችግኝ ተከላው የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረገገጥ፣ የአየር ጠባይን ለመቆጣጠር ብሎም ሀገራችንን የቱሪስት መስሕብ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደረግ ስለሆነ ይህን መሰሉን መርሀ ግብር ባንኩ አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚሠራ ገልጿል፡፡
ባንኩ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮችን ያካሄደ ሲሆን ይህም ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያበረከተ የሚገኘው አስተዋፅኦ አካል ነው፡፡