የመጀመሪያ ዙር የተጨማሪ አክሲዮን ሽያጭ መጠናቀቁን ስለማብሰር
የሕብረት ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 12ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተጨማሪ አክሲዮን የመጀመሪያ ዙር ሽያጭ እንዲካሄድ በወሰነው መሰረት በባንኩ የሃያ አምስት አመት ታሪክ ውስጥ በአጭር ጊዜ በ60 ቀን የጊዜ ገደብ ውስጥ በተከናወነ የአክሲዮን ሽያጭ ዋጋቸው 6.4 ቢሊዮን ብር (ስድስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር) የሆኑ አክሲዮኖች ከዋጋቸው አንድ አራተኛ እና ከዚያ በላይ ክፍያ ተፈፅሞባቸው የተሸጡ እና የአክሲዮን ሽያጩ እ.ኤ.አ.31 ጃንዋሪ 2024 (ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም.) መጠናቀቁን በደስታ እየገለፅን ለባንኩ ባለአክሲዮኖች ፣ የቦርድ ዳይሬክተሮች እና የባንኩ ስራ አመራር እንኳን ደስያለን እንላለን።
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!