|

የአቶ መላኩ ከበደ ከሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መልቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አቶ መላኩ ከበደ፣ ከሃያ ዓመታት አገልግሎት በኋላ ከነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ .ም. ጀምሮ ከሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ስንገልፅ፣ ኃዘን የሚሰማን ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚ በባንኩ በነበራቸው ቆይታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አቶ መላኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በነበሩበት ወቅት ለሕብረት ባንክ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፣ በአመራር ዘመናቸው የባንኩን ሥራ በማስፋፋት፣ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስልታዊ አጋርነትን በመፍጠርና የባንኩን ገቢ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡ ባንኩ በርሳቸው የአመራር ጊዜ ከመሪ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ አሁንም ለቀጣይ ስኬት በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል፡፡

የዲሬክተሮች ቦርድ ፣ አቶ መላኩ በባንኩ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ላሳዩት የሥራ ተነሳሽነት፣ ለነበራቸው ራዕይና ለባንኩም ሆነ ለመላው ባለድርሻ አካላት ላደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ ልባዊ ምሥጋናውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም፣ የሕብረት ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ፣ አቶ መላኩ በወደፊት ሕይወታቸው መልካም የሆነው ሁሉ እንዲገጥማቸው ከልብ ይመኛል፡፡

የዲሬክተሮች ቦርድ
ሕብረት ባንክ

Similar Posts