የወንድና የሴት ጥበቃ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) – ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ሕባ/007/16- የጨረታ ማስታወቂያ:: ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ አይነት የወንድና የሴት ጥበቃ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | ዝርዝርመግለጫ | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
1 | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) ፐርፕል ቀለም | ሜትር | 1,830.50 | |
2 | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) ተርኪሽ ቀለም | ሜትር | 1,830.50 | |
3 | ሸሚዝ ፐርፕል ቀለም | በቁጥር | 523 | |
4 | ሸሚዝ ተርኪሽ ቀለም | በቁጥር | 523 | |
5 | ጫማ ጥቁር ቀለም (ለወንድ) | በጥንድ | 466 | |
6 | ጫማ ቡኒ ቀለም (ለወንድ) | በጥንድ | 466 | |
7 | ጫማ ጥቁር ቀለም (ለሴት) | በጥንድ | 57 | |
8 | ጫማ ቡኒ ቀለም (ለሴት) | በጥንድ | 57 | |
9 | ካልሲ | በጥንድ | 932 | |
10 | የጥበቃ ካፖርት | በቁጥር | 141 |
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሀምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- እያንዳዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከህብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 67 32 08 ወይም 011 470 6541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡