የግል ባንኮች የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ክፍል ኃላፊዎች ማሕበር 20ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን አከበረ፡፡

20ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ <<ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል!>> በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ የግል ባንኮች የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ክፍል ኃላፊዎች ማሕበርም ይህንኑ በዓል ሕዳር 21 ቀን 2016 ዓ/ም በሕብረት ባንክ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብሯል፡፡

የበዓሉን አከባበር በንግግር የከፈቱት የግል ባንኮች የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ክፍል ኃላፊዎች ማሕበር ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ኃይለመስቀል በየባንኩ በቀላሉ የማይገመት የሕዝብ ሀብት በሙሰኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንደሚባክን ገልጸው በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚገኙ የስራ መሪዎችና ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ብሎም በሀገር ደረጃ የሚካሄደውን የጸረ ሙስና ትግል መደገፍ የሚችሉበት የጋራ ማህበር መመስረቱን ተናግረዋል፡፡

የማሕበሩ አባል አቶ ጥላዬ እንየው የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱን መነሻ በማድረግ ሙስናን መከላከል በሚቻልባቸውና በባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ላይ የተለያዩ የግል ባንኮች የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts