የጨረታ ማስታወቂያ – የጨረታ ቁጥር ሕባ/037/14
ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ አይነት የወንድና የሴት ጥበቃ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | ዝርዝርመግለጫ | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
1 | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) የጨርቅ ቀለም ፐርፕል | በሜትር | 1,757 | |
2 | ብትን ጨርቅ (ሱፍ) የጨርቅ ቀለም ተርክሽ | በሜትር | 1,757 | |
3 | ሸሚዝ ፐርፕል ቀለም | በቁጥር | 1,066 | |
4 | ሸሚዝ ተርክሽ ቀለም | በቁጥር | 502 | |
5 | ጫማ ጥቁር ቀለም (ለወንድ) | በጥንድ | 441 | |
6 | ጫማ ቡኒ ቀለም (ለወንድ) | በጥንድ | 441 | |
7 | ጫማ ጥቁር ቀለም (ለሴት) | በጥንድ | 61 | |
8 | ጫማ ቡኒ ቀለም (ለሴት) | በጥንድ | 61 | |
9 | ካልሲ (ለወንድ ) | በጥንድ | 908 | |
10 | የጥበቃ ካፖርት | በቁጥር | 64 |
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- እያንዳዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8.45 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከህብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 67 32 08 ወይም 011 470 6541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡