|

2ተኛው ዙር የሕብረት ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” …

2ተኛው ዙር የሕብረት ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሎተሪ ዕጣ ሰኔ 02/ 2014 ዓ.ም በደማቅ ስነ ስርዓት በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ወጥቷል፡፡

ሕብረት ባንክ ላለፉት አምስት ወራት ከታህሳስ 6 እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2014 ዓ/ም የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግ ብሎም የባንኩን የተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግ በማለም ያዘጋጀው የ”ይቆጥቡ፤ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ“ መርሃ ግብር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ሰኔ 02/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በእጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ የስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ የስትራቲጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱአለም ሐይሉ መርሃ ግብሩ የቁጠባ ባህልን ከማሳደግ ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ ረገድ ለኢኮኖሚው የራሱን ድርሻ የሚያበረክት መሆኑን ጠቅሰው ሕብረት ባንክ እንዲህ አይነቱን የማበረታቻ ሽልማት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሕብረት ባንክ ለእድለኞቹ የአውቶሞቢል፣ የባለ 3 እግር ባጃጆች፣ ባለ 43 ኢንች ቴሌቭዥኖች፣ ፍሪጆች የልብስ ማጠቢያ ማሽኖችና የዉሀ ማጣሪያ ማሽኖችን ያዘጋጀ ሲሆን በቅርቡም ባንኩ ለባለእድል ደንበኞቹ ሽልማቶቹን በይፋ እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡

ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ

Similar Posts