22ኛው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሕብረት ባንክ ተከበረ









22ኛው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሕብረት ባንክ ተከበረ
የሕብረት ባንክ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች 22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር!” በሚል መሪ ቃል ሕዳር 23/2018 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብረዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ሕብረት ባንክ ሙስናን ለመዋጋት የሚያስችሉ ደንቦችንና መመሪያዎችን በመቅረፅ፣ ሥራ ላይ በማዋልና በጥናት የተደገፉ መፍትሄዎችን በመስጠት የተጠናከረ ሥራ እየሰራ ይገኛል።
አቶ ንጉሱ አክለውም ሕብረት ባንክ በቀጣይም ሙስናን በተቀናጀ ሁኔታ በመዋጋት በአለም አቀፍ ብሎም በሀገር ደረጃ ለሚደረገው እንቅስቃሴ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በዕለቱ የሕብረት ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ሃብታቸውን በማስመዝገብ እና ቅጹን በጉባኤው ፊት በማስረከብ አርአያነታቸውን ያሳዩ ሲሆን ተሰብሳቢዎችም ለመርሀግብሩ መሪቃል ተፈጻሚነት እንደሚተጉ ቃል በመግባት ፕሮግራሙን አጠናቀዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ የሕብረት ባንክ የሥራ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!