የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
| ተራ ቁ. | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1. | ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማ/ | ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግ/ማ/ | ሸገር | አዲስ አበባ ከተማ፣አራዳ ክ/ከተማ፣ወረዳ 09፣የቦታ ስፋት 852.6 ካ.ሜ አገልግሎት ለድርጅት የሆነ በግንባታ ላይ ያለ G+7 (ባለሰባት ፎቅ ሕንፃ)፤ | አ/ሊዝ/17/08/6362/01 | 355,897,544.00 | ኅዳር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 2. | አቶ ዳግም ከበደ ከቻራ | ዶ/ር ከበደ ከቻራ ሸዋ | ዓለም ባንክ | አዲስ አበባ፣ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 06፣የቦታ ስፋት 667 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለድርጅት (ንግድ)የሆነ G+ 6 ሕንፃ፤ | AA000060603587 | 123,911,020.00 | ኅዳር 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 3. | አቶ አረጋ እንድሬ አለማው | አቶ አረጋ እንድሬ እና ወ/ሮ ፈለቁ ደምሴ | ኮተቤ | አዲስ አበባ ከተማ፣የካ ክ/ከተማ፣ወረዳ 09፣የቦታ ስፋት 191 ካ.ሜ የሆነ ለመኖሪያ አገልግሎት የሆነ ሰርቪስ ያለው G+2 (ባለሁለት ፎቅ) ቤት፤ | AA000050901646 | 19,012,714.00 | ኅዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 4. | ባርሳቤ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | መብቶም ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | ቃሊቲ | አዲስ አበባ ከተማ፣አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ወረዳ 05፣የቦታ ስፋት 1942 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለኢንደስትሪ የሆነ ቤት | አቃ/ቃ/ክ/ከ/ሊዝ/ጨ/062/2 | 23,965,040.00 | ኅዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5:00 እስከ 6:00 ሰዓት |
| 5. | ወ/ሮ አሳቤ ጫኔ ይርዳዉ | ወ/ሮ አሳቤ ጫኔ ይርዳዉ | ቃሊቲ | ኦሮሚያ ክልል፣ሸገር ከተማ፣ሱሉልታ ክ/ከተማ፣ወረዳ QW ፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት | Sul/1916/15 | 3,658,755.00 | ኅዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 6. | አቶ አቡሳድ ነሻ አህመድ | አቶ ነሻ አህመድ አልይ | ሕብር ታወር | አዳማ ከተማ፣ቀበሌ 03፣የቦታ ስፋት 1709 ካ.ሜ የሆነ ለመጋዘን አገልግሎት የሚውል | 2110/2000 | 17,183,808.00 | ኀዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 7. | ኔይሎስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግ/ማ/ | ኔይሎስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | ቦምብ ተራ | ባህርዳር ከተማ፣ዳ/ሚኒሊክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14(ግንቦት 20) የቦታ ስፋት 15,000 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለኢንደስትሪ የሆነ ህንፃ፤ | ባህኢፓ/0162/11 | 13,848,880.00 | ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
| 8. | አቶ አዲሱ አላምኑ ካሳ | አቶ አዲሱ አላምኑ ካሳ | እንጅባራ | እንጅባራ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 201.972 ካ.ሜ፣ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት | AM010011605026 | 2,180,981.00 | ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት |
| 9. | አቶ አደራጀው ታረቀኝ ጎሸ | አቶ አደራጀው ታረቀኝ ጎሸ | ፋሲል | ጎንደር ከተማ፣አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 19፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ የሆነ፣ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት | 9903/06 | 6,421,513.00 | ኅዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
- ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ ከተራ ቁጥር 5-6 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ነው፡፡ ከተራ ቁጥር 7-8 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በባህርዳር ከተማ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና (ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በተራ ቁጥር 9 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው ጎንደር ከተማ በሚገኘው የባንኩ ፋሲል ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ነው፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡ ሸገር ቅርንጫፍ፡ 011 126 54 62፣ አለም ባንክ ቅርንጫፍ፡ 011 369 47 79፣ ኮተቤ ቅርንጫፍ: 011 667 52 54፣ ቃሊቲ ቅርንጫፍ፡ 011 462 62 01፣ ሕብር ታወር ቅርንጫፍ 011 557 54 47፣ ቦምብ ተራ ቅርንጫፍ፡ 011 278 17 28፣ እንጅባራ ቅርንጫፍ፡ 058 227 18 22፣ ፋሲል ቅርንጫፍ፡ 058 111 68 70 ወይም የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ 011 470 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!